undefined undefined undefined undefined

    Get Appointment

    CircleCircle
    BlogJuly 3
    በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ፣ የጸጥታ አካላትን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ነው። በዩኒቨርሲቲው መምህርና ተመራማሪ እንድዉም የአረንጓዴው አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አስተባባሪ የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር ሶሬሳ ሹማ እንደተናገሩት ሀገራችን በአሁኑ ወቅት በችግኝ ተከላ ላይ ትኩረት አድርጋ እየሰራች መሆኗን ገልጸዋል፡፡ ፍሬያቸዉ ለመብል በምያገለግሉ ችግኞች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም በመናገር እኛም በበኩላችን የዜግነት ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን በማለት ተናግሯል።
     
    የዩኒቨርሲቲው ተ/ፕሬዝዳንት ታደሰ ረጋሳ (ፒኤች.ዲ) እንደተናገሩት የዛሬው የችግኝ ተከላ ተነሳሽነት ከመንግስት አቅጣጫ ጋር የተጣጣመ መሆኑን በመግለጽ ፍሬያቸዉ ለምግብነት የሚውሉ ችግኞችን የማልማት ስራ ለዛሬ ብቻ የምገደብ ሳይሆን ለወደፊትም የማህበረሰባችንን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትጋት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
     
    በመጨረሻም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ም/ቴ/ሽ/ና ማ/አ/ም/ፕሬዝዳት ተወካይ የሆኑት ረዳ ነሞ (ፒኤች.ዲ) ዩኒቨርሲቲዉ በጥናት ላይ የተመሠረተ የማህበረሰብ አገልግሎት ላይ እንደምሳተፍ በመናገር ህብረተሰቡ የተተከሉ ችግኞችን እንዲንከባከበው አሳስበዋል።