ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ከዳይሬክቴሮችና ከዲኖች ጋር ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች(Key Performance Indicators) ውል ስምምነት ተፈራረመ።
ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ስራን በውጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችል የስራ ውል ስምምነት (Performance Contracting Agreement) መፈራረሙን ተከትሎ በዛሬዉ እለት ማለትም ታህሳስ 21/2017 ዓ.ም ሁለቱ ም/ፕሬዝዳንቶች ከፕሬዝዳንቱ ጋር ከተፈራረሙ በኃላ ከዳይሬክቴሮች፣ከሥራ አስፋጻሚዎች እና ከዲኖች ጋርም ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች ተግባራዊና ዉጤታማ የምሆንበት ላይ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
በስምምነቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ረዳ ነሞ እንደተናገሩት የቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች(Key Performance Indicators) ስምምነት ዩኒቨርሲቲያችን በሀገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ጠንካራ ተቋም እንዲሆን ይረደናል ብለዋል ።
ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾችን ዓላማ፣ ይዘት፣ ክትትልና የትግበራ ሂደቶች ላይ ለተሳታፍዎች አጭር ገለጻ ያቀረቡት ደግሞ የስራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ጨራ በቀለ ስሆኑ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች በማንና በምን ስልት ልተገበር እንደምቹሉ አብራርቷል ፡፡ ከገለጻው በኋላ አስተያየታቸውን እና ምክረ ሃሳባቸውን ያካፈሉ ተሳታፍዎቹ በሃላፊነት እና በጽናት በመሥራት የዩኒቨርሲቲዉን እቅድ በተሳካ ሁኔታ ማሳካት እንደምቻል ገልጸዋል።
የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ዶ/ር ገመቹ ብርሃኑ ራዕያችንን እውን ማድረግ የምንችለው በጋራ ጥረት እና እንደ ዩኒቨርሲቲ የተቀመጡ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾችን በማሟላት እንደ ዩኒቨርሲቲ ቁርጠኝነታችንን በማጎልበት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ተ/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ረጋሳ ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾች ለአንድ ተቋም እድገትና መልካም ገጽታ ላይ ያላቸዉን ጉልህ አስተዋፅኦ አበክረው ገልፀዋል።ሁሉም የሥራ ክፍሎች ተቋማዊ ተልእኳቸው በመወጣት ዩኒቨርሲቲው ራስን በራስ የማስተዳደር እያደረገ ያለዉን ጉዞ ለማሳካት የተሰጣቸዉን ተቋማዊ አደራ በቁጠኝነት መወጣት እንዳለባቸዉም አሳስበዋል።