የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የደምቢ ዶሎ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ
(የካቲት 28/2017 ዓ.ም ) የኢ.ፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ፣ የምንስትሩ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሃላፍ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝታቸዉ ወቅትም የዩኒቨርሲቲዉ ሞዴል ትምህርት ቤት የሆነዉ የዶ/ር ነጋሶ ግዳዳ ልዩ ትምህርት ቤትን ስጎበኙ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እየተሰራ ያለዉ ስራ ዩኒቨርሲቲዎች ተወዳዳሪ እንድሆኑ እያደረጋቸዉ ነዉ ያሉት ፕሮፌሰሩ ተማሪዎችም ለተሸለ እዉቀት መመራመርና ማንበብ እንደምጠበቅባቸዉ ጠቁመዉ ለበለጠ እዉቀት የምተጋ ትዉልድን ማፍራት አለብን ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያ ልጆች ከልጂነታቸዉ ጀምረዉ እንድተዋወቁና አንድነታቸዉን የምያጠናክር የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን በሃገር ደረጃ በመገንባት ከሁሉም የአገርቱ ክፍል የተወጣጡ ልጆች በአንድ ትምህርትቤት የምማሩበት እድል እንፈጥራለን ብለዋል፡፡
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሃላፍ፣ ዶ/ር ቶላ በሪሶ በበኩላቸዉ ለትምህርት ጥራት ቅድሚያ በመስጠት የአካዳሚክ ብቃትና ጠንካራ ስነምግባር ያላቸውን ተማሪዎች ለማፍራት እና ለሀገር እድገት አስፈላጊ የሆነውን የሰው ሃይል በማልማት ላይ ትምህርት ቤቶች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት እንዳለባቸዉ አመልክተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በዩኒቨርሲቲው የተቀናጀ የግብርና ምርምር ማዕከሉ ዉስጥ እየተሠሩ ያሉ የልማት ቱሩፋቶች በተለያዩ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ በእንሰት ምርት፣ በእንሰሳት እርባታ በዓሣ ምርት፣እና በሌሎችም ማህበረሰቡን ተጠቃሚ እደረገ ያለዉ ተስፋ ሰጪና አበረታች መሆኑንና ዩኒቨርሲቲዉ በምግብ ግባዓቶች ራሱን ለመቻል ጥረት እያደረገ መሆኑንም ተመልክቷል፡