ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ስያስተምር የነበረ 1059 ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ::በተማሪዎች ምርቃት ስነ-ስርዓት ላይ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል እንግዶች እንዲሁም የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ተገኝቷል፡፡ በዝህ ምርቃት ላይ 760 መደበኛ ተማሪዎችና መደበኛ ያልሆኑ 299 በአጠቃላይ 1059 ተማሪዎችለመጀመሪያ ጊዜ አስመሪቋል፡፡

በክብር እንግዳነት በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል የውሃ ሀብት ልማት እና ኢነርጂ ብሮ ሀላፍ የሆኑ ዶ/ር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢታና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕት ሲያስተላልፉ ተመሪቃችሁ ወጥታችኋል ማለት ትምህርት ጨርሳችኋል ማለት ሳይሆን ለሚቀጥለው የትምህርት ዕድል ራሳችውን ማዘጋጀት እንዳለበቸው መልዕክታቸውን አስተላልፏል፡፡ በተጨማሪም የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ በዝህ መርሃ ግብር ላይ እንዳሉት ከብዙ ድክመት በኋላ የልፋታችሁን ፍሬ ስላገኛችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብሏል፡፡ በማከልም ለዝህ ለመማር ማስተማር ስኬት ጉልህ ሚና ለተወጡት አካላት ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡