የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አማካሪ ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አማካሪ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ባስቀመጠው መመሪያ መሠረት የጠቅላላ ጉባዔውን ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት በተገኙበት ውይይቱን አካሄዷል፡፡
ምክርቤቱ ለዩኒቨርሲቲያችን ሰላም ከማህበረሰቡ ጋር እን
ሰራለን በሚል ርዕስ ያካሄደ ሲሆን በውይይቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ሲሆን በመክፈቻ ንግግራቸውም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው የመማር ማስተማር ሂደቱን መልሶ ለማስጀመርና ተመራቂ ተማሪዎችን በመጀመሪያ ዙር ለመቀበል መጠነ ሰፍ ዝግጅት ማድረጉን ገልጾል፡፡ በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ እንዳሉት የመማሪ ማስተማሩን ሂደት ሠላማዊ ለማድረግ ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡
የምክር ቤት አባላትም በውይይቱ ላይ እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቡን በማሳተፍ የሚሰራውን ስራ ጠንክሮ መቀጠል እንዳለበት በማንሳት በማንኛውም ግዜ ማህበረሰቡ ከዩኒቨርሲቲው ጎን እንደሚቆም አሳውቋል፡፡ በውይይቱ መጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 29 እና 30 2013 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው እንደሚገቡ በማስታወስ ደማቅ አቀባበል ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ኮሚቴ አዋቅሮ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል፡፡