ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ በቄለም ወለጋ ዞን ስር ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

የድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ለታ ተስፋዬ ሲሆኑ በንግግራቸውም አሁን ያለንበት ጊዜ ትውልድን ለማብቃት ሁሉም መስራት ያለበት ጊዜ ላይ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ጊዜ የትምህርት ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች ድጋፍ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የቄለም ወለጋ ዞን ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፍዎች በተገኙበት ድጋፍ አድርጓል፡