ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙርያ ስልጠና ሰጠ

ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙርያ ስልጠና ሰጠ

ብቁ ሴቶችን ማፍራት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ለዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ሰቷል፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ስልጠናውን ያስጀመሩት የዩኒቨርስቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ቡሊ ዮሀንስ ሲሆኑ በንግግራቸውም ተማሪዎቹ ከቤት የወጡበት ትልቁ አላማቸውን እንዳይዘነጉና ትምህርታቸው ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ በመጠየቅ በዝህ ረገድ የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲም አስፈላጊውን ዕገዛ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ሴት ተማሪዎቻችን ባገኙት ጥሩ አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም ከራሳቸው አልፎ ለሁሉም መትረፍ እንዳለባቸው በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑ ወ/ሮ ህብረት በቀሌ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲውከዝህ በፍት በተለያዩ ጊዜ በተለያዩ ጉዳዩች ላይ ለሴት ተማሪዎች ስልጠናዎችን መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡